የጌታን ልደት(ገናን)በቤተልሔም
9 ቀናት - 7 ለሊት (የጉዞ ቀናቶችን ጨምሮ)
$1,280
የገናን በዓል ጌታ በተወለደበት ቦታ በቤተልሔም ያክብሩ። የእምነትዎ መሰረት የሆኑትን ቅዱሳን ቦታዎችንም ይጎብኙ።
ጠቅላላ የጉዞ መረጃ
የገና በዓል ጉዞ ከፍተኛ ህዝብ የሚበዛበት ወቅት በመሆኑና በዓሉንም በጥሩ ሁኔታ ለማክበር ከፍተኛ ጥረትን የሚጥይቅ በመሆኑ ድርጅታችን ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የሚያወጣቸውን የጉዞ መርሃ ግብር በአጽንኦት ይከታተሉ።
DAY 1
ወደ ቅድስት ሃገር ጉዞ መነሻ
DAY 2
እስራኤል የሚገቡበት ቀን
የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና ወደ ሆቴል ጉዞ
እረፍት በሆቴል
Day 3
ደብረ ዘይት ተራራ ፤ ጌቴሴማኒ
የቅድስት ድንግል ማርያምን መካነ መቃብር
ጎሎጎታ
Day 4
ቤተ ልሔም
ኢን ኬሬም
የገና የለሊት ቅዳሴ
Day 5
የገና ክብረ በዓል
ዕረፍት
Day 6
ኢያሪኮ
የዮርዳኖስ ወንዝ
የጨው ባህር
Day 7
ቅፍርናሆም
ታብጋህ - የተራራው ስብከት
የጀልባ ጉዞ በገሊላ ባሕር
Day 8
ቃና ዘገሊላ ፤ ናዝሬት ፤ ደበረ ታቦር
ሐይፋ
የነቢይ ኤልያስን ባዕት/ዋሻ
Day 9
ወደ ሀገራችሁ የምትሸኙበት ቀን
በዚህ የጉብኝት መርሐ ግብር ውስጥ የተካተቱት ዋና ዋና ቅዱሳዊ ቦታዎችን ብቻ ሲሆን ፣ በጉዞኣችን በርካታ እዚህ ውስጥ ያልተጠቀሱ ቅዱሳዊ ቦታዎችን እንጎበኛለን።
Day 1 የጕዞ መነሻ
በዚህ ዕለት ጕዞ ወደ ቅድስት ሀገር የሚደረግበት ቀን ይሆንና፣ በነገታው ኢየሱስ ክርስቶስ እግሮቹ በተመላለሱበት ምድር እርሰዎም ይራመዳሉ።
የአየር በረራዎ መነሻና እስራኤል መድረሻዎ በአንድ ቀን ከሆነ የሚነሱት በሚቀጥለው ቀን ይሆናል።
Day 2 ሰላምታና የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል!
በዚህ ዕለት ቤንጎርዮን የእስራኤል አየር ማረፊያ ያርፋሉ፤ በዚያም የአፍሮ ኢየሩሳሌም አስጎብኚ ድርጅት የሥራ ባልደረቦች ልባዊና መልካም የሆነ አቀባበል ያደርጉለዎታል። በቀጥታ ኢየሩሳሌም ወደ ያዝንለዎት ሆቴል እንወስደዎትና እራትና የእረፍት ጊዜ ያደርጋሉ። አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
Day 3 ደብረ ዘይት ተራራ፣ ጌተሰማኒ ፣ ጎሎጎታ
ከቍርስ በኋላ ጉዞአችንን ቅዱስ ቦታ በሆነው በደብረ ዘይት (2ሳሙ15፣30 ማር 11፣1 ሐዋ 1፣12) ጕብኝታችንን እንጀምራለን።
እዚያ እንደደረስንም አስቀድመን ኢየሱስ ያረገበትን ሥፍራ - የዕርገት ቤተክርስቲያንን እንጎበኛለን። ከዚያም ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ "አባታችን ሆይ" የሚለውን ጸሎት ያስተማረበትን ቦታ ፓተር ኖስተር ቤተክርስቲያን (ኢልዮና)ን እንጎበኛለን። ደብረ ዘይት ተራራ አናት ላይ ሆነን ከርቀት የጥንታዊቷን የኢየሩሳሌም ውብ መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንም ደስ እንሰኛለን፣ ከደብረ ዘይት ተራራ ቍልቍል እንወርድና ጌታ ኢይሩሳሌምን ዐይቶ ወዳለቀሰላት(ሉቃ 19፡ 41-44) ወደ ዶሚንዮስ ፍለቨት የጸሎት ቦታ እናመራለን። ኢየሱስ ሲጸልይ ወደ ተያዘባት ወደ ጌቴሴማኒ ያትክልት ስፍራ(ማቴ 26፣ 36-58/ ሉቃ 26፡ 36-58) ወደ ታዋቂው የሕዝቦች ሁሉ ቤተክርስቲያን ጉዞኣችን እንቀጥላለን። በመቀጠልም የቅድስት ድንግል ማርያምን መካነ መቃብር ከጎበኘን በኋላ የምሳ እረፍት እናደርጋለን።።
በመቀጠልም ኢየሱስ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የነበረውን ሰው የፈወሰባትንና የመጠመቂያ ሥፍራ የነበረባትን ቤተ ሳይዳን/ቤተ ስዳ/ በመጎብኝት እን (ዮሐ 5፣ 2-9)። ከዚያም ቪያ ዶሎሮሳ የተባለውንና ኢየሱስ ካባድና ፅኑ ጸዋትወ መከራ ያለፈበትን ባለ 14 ጣቢያ መንገድ ከጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ እንጀምርና ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታ በጎልጎታ ላይ ጕዞአችንን እናብቃለን። ራትና አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
የእለቱን ጉዞኣችንን የምናበቃው በደብረ ዘይት ተራራ ያሉትን ቅዱሳዊና ታሪካዊ ቦታዎችን በመጎብኘት ይሆናል። በዚያም ጌታ የደቀ መዛሙርቱን እግር ወዳጠበበትና ከነርሱም ጋር የመጨረሻዋን የፋሲካን ራት ወደበሉበት ደርብ/ቤት እናቀናለን(ዮሐ13፡4)፤ ከዚያም ወደ ንጉሥ ዳዊት የመቃብር ሥፍራና ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘላለም ወዳሸለበችብት ወደ ዶርሚሽን ቤተክርስቲያን እንቀጥላለን። በጽዮን በር በኩል ወደ ጥንታዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ እንገባና የአይሁድ ብቸኛ ቅዱስ ቦታ፣ ለሙስሊሞች ደግሞ ሦስተኛው ቅዱስ ቦታ የሆነውን ምዕራባዊውን የቤተ መቅደስ ክፍል ከጎበኝን ብኋላ ወደ ሆቴላችን እንመለሳለን::
Day 4 ቤተ ልሔም፣ ኢን ኬሬም
በዚህ ዕለት ከቍርስ በኋላ ጉዞአችንን ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ቤተልሔም ይሆንና፣ በባሲልካ ኔቲቪቲ ምልክት የተደረገበትን የኢየሱስን የልደት ቦታ እንጎበኛለን(ሉቃ 2፣ 1-7)። መልአከ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ብሎ ለእረኞች የጌታን ልደት ያበሠረበትን፣ መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩበትን ሥፍራ(የወተት ዋሻ)ን እንመለከታለን( ሉቃ2፡8-18)። ከሰዓት በኋላ የመጥምቁ ዮሐንስን የልደት ቦታ ዔይን ካሬምን እንጎብኛለን። ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጎብኝት የሄደችበት ሀገርና ከእርሷም ጋር የተገናኘበትን ሥፍራ ላይ ያልውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን(ሉቃ1፡39-80)። የካህኑ የዘካሪያስና ኤልሳቤጥ ቤት፣ የማሪያምንም ምንጭ እንመለከታለን። በፍጻሜውም መጥምቁ ዮሐንስ በይፋ አግልግሎት የጀመረበትን ምድረበዳ እንጎበኝና ለእረፈት ወደ ሆቴላችን ተመልሰን ለልደት የበዓል ዋዜማ ምሽት ዝግጅት እናደርጋለን፡፡
በምሽትም የገናን የለሊት ቅዳሴን ለመሳተፍ ኢየሱስ ወደ ተወለደባት ትክክለኛ ቦታ ወደ ቤተልሔም እንጓዛለን፡፡
Day 5 ዕለተ ሰንበት- የልደት ክብረ በዓል - ነጻ የግብይት ቀን
የዛሬን የገናን ቀን እስከ ምሳ ሰዓት በሆቴላችን እረፍት ካደርግን ብሗላ በዓሉን ተሰባስበን የምሳ ፕሮግራም አድርጋለን። ከቀትር በሗላ በኢየሩሳሌም አካባቢ ያልጎበኘናቸው ቦታዎች ካሉ ጉብኝት እናደርጋለን። እራትና አዳር በኢየሩሳሌም ይሆናል።
Day 6 ኢያሪኮ፣ የዮርዳኖስ ወንዝና ሙት ባሕር
ቀኑን አስገራሚ መልክዐ-ምድራዊ አቀማመጥና ገጽታ ያለውን የይሁዳ ምድረ በዳን እየተመለከትን ዜኬዎስ የወጣበትን የሾላ ዛፍና የኤልያስን ምንጭ ወደ ምንመለከትበት ወደ ኢያሪኮ በመጓዝ እንጀምራለን። ኢየሱስ በሰይጣን ወደ ተፈተነበት ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ እንወጣለን። ከዚያም ኢየሰስ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀበትን ልዩ የዮርዳኖስ ወንዝ ቦታ፣ ካሰር አል-ያሁድ እንጎበኛል። በደቡባዊው የሙት ባሕር ዳርቻ ወደ ምትገኘው፣ በዓለምም ካባሕር ጠለል በታች 400 ሜትር የመጨረሻው ረባዳ ቦታ ወደ ሆነው ወደ ጨው ባህር እንጓዛለን። በዚያም በዓለም እጅጉን በታወቀውና በጨው ማዕድን በበለጸገው ውሃ ወስጥ እንዝናናለን።
በመጨረሻም ጉዞኣችንን ወደ ሰሜን በማድረግ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናቶች በዚያ ያሉትን ቅዱሳዊና ታሪካዊ ቦታዎችን ለምጎብኘት በገሊላ አካባቢ ወደትያዘልን ሆቴል እናመራለን።
Day 7 የገሊላ ባህርንና አካባቢው
ከቍርስ በኋላ ጉዞአችንን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የመጠመቂያ ቦታ እናደርጋለን። ከዚያም ኢየሱስ የተራራውን ስብከት (አንቀጸ ብጹዓን) የሰበከበትን ተራራ እንጎበኛለን(ማቴ 5፡7)። በመቀጠልም ኢየሱስ አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ አበርክቶ ለሕዝቡ ወደ መገበበት ቦታ(ማቴ 14፡14-43) ወደ ታብጋ እንሄድና የ4ኛው ክ/ዘመን የሞዛይክ ጣራ ያለውን ቸርች ኦፍ መልቲፕልኬሽን /የበርክቶ ቤተክርስቲያን/ን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ናዝሬትን ትቶ በመምጣት መኖሪያው ያደረገባትንና በምድር ላይም አገልግሎቱን ወደ ጀመረባት በዘልማድም የኢየሱስ ከተማ እየተባለች ወደ ምትጠራው ወደ ቅፍርናሆም እናልፋለን። በዚያም በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ምኲራብንና የቅዱስ ጴጥሮስ መኖሪያ የነበረውን ቤት እንጎበኛለን። በምሳ ሰዓት ግሩም የሆነውን የቅዱስ ጴጥሮስን ዓሣ እንመገብና በጀልባ ላይ ተሳፍርን ኢየሱስ በእግሩ የተራመደበትን የገሊላን ባሕርን እንሻገራለን(ማቴ14፡22-23)። በዘመነ ኢየሱስ የነበረውን የዓሣ አጥማጅ ጀልባ፣ "የኢየሱስ ጀልባ"ን በኪቡጽ ጊኖሣር እንጎበኛለን። ለራትና ለአዳር ወደ ሆቴላችን እንመለሳለን።
Day 8 ደበረ ታቦር፣ ቃና ዘገሊላ፣ ናዝሬት ፣ የኤልያስ ባዕት(ዋሻ)፣ ሐይፋ
የዕለቱን ጕዟችንን በታችኛው የገሊላ ክፍል በኩል በማድረግ የኢይዝራዔልን ሸለቆንና ብሎም እንደ ዮሐንስ ራዕይ መሠረት የሰውልጆች የመጨረሻው ጦርነት የሚደረግበትን የሚግዶን አስደሳች መልክዐ-ምድራዊ ገጽታን እየተመለከትንና ደስ እየተሰኘን በቀጥታ ጌታ ብርሃነ-መለኮቱን ወደ ገልጠበት ወደ ደብረ ታቦር እናመራለን። ኢየሱስ በሰረግ ቤት ታድሞ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ የመጀመሪያውን ተአምራት ያደረገበትን(ዮሐ 2፡1-11)ቃና-ዘገሊላንና በዚያም የሚገኘውን ቤተክርስቲያን እንጎበኛለን። በመቀጠልም ወደ ናዝሬት በማምራት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደስ ይበልሽ በማለት የኢየሱስን መወለድ ለድንግል ማርያምን ያበሠረበትን(ሉቃ 1፡26-38) ጥንታዊውን የብሥራት ዋሻን እንጎበኛለን። የዮሴፍን ቤትን እንመለከትና ወደ ማሪያም ምንጭ እንሄዳለን ።
በመቀጠልም የቀርሜሎስ ተራራ"የእግዚአብሔር የወይን ተክል"ንና የታላቁ ነቢይ የኤልያስን ባዕት/ዋሻ ለመጎብኘት ወደ ሐይፋ እናመራለን። ከዚያም በሐይፋ የሚገኝውንና ከፍ ካለው መልክዐ-ምድራዊ ገጽታ ላይ የተንጣለለውን፣ ባትክልትም የተዋበውን የባሂኢን ያምልኮ ሥፍራ ተመልክተን ወደ ቴል አቪቭ በሚወስደው በሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ መንገድ ኣድርገን ወደ ጃፋ እናመራለን። በዚያም ነቢዩ ዮናስ ከእግዚአብሔርና ከትእዛዙ ለመኮብለል መርከብ የተሳፈረበትን ቦታና(ዮና 1፡3) ብሎም ደግሞ ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው የወጣበትን የቍርበት ፋቂው የስምዖን ቤት(ሐዋ 10፡9-19) ፣ጥንታዊቷንም የጃፋን ወደብ እንጎበኛለን። አዳራችን በኢየሩሳሌም ይሆናል።
Day 9 የጕዞ መመለሻ ቀን
ወደ ኤርፖርት በመሄድ ወደ ሀገራችሁ የምትሸኙበት ጊዜ ይሆናል።
* * * * *
ክፍያው የሚያጠቃልለው (INCLUDED)
ሆቴል ለ7 ወይም ለ9 ለሊት
ቁርስ ምሳ እራት (ብፌ)
ትራንስፖርት ከአየር ማርፊያ (በግሩፕ ለሚገቡ ብቻ)
የቅዱሳዊ ቦታዎች ጉብኝት በዘመናዊ አውቶቡስ
አማርኛ ተናጋሪ አስጎብኚ
የጉብኝት ቦታዎች የመግቢያ ከፍያዎች
ክፍያው የማያጠቃልለው (EXCLUDED)
አለም አቀፍ የአየር በረራዎች (ለጥሩ የቲኬት ዋጋ ያነጋግሩን)
ለአስጎብኚ እና ለአውቶቡስ ሾፌር የሚሰጡ ቲፖች
ከአየር ማረፊያ ትራንስፖርት በግላቸው ለሚመጡ (ለማዘዝ ያነጋግሩን)
የጉዞ ኢንሹራንስ
ከምግብ ጋር የሚወሰዱ ተጨማሪ መጠጦች
"ከፍያው የሚያጠቃልለው" ውስጥ ከተዘረዘሩት ውጭ ማንኛውም አገልጎት
ሊያውቁት የሚገባ:
** ሆቴል በክፍል ሁለት መኝታ ይኖረዋል (Double Room Occupancy)
** ለብቻ የመኝታ ክፍል ለማዘዝ በቅድሚያ ያነጋግሩን (Single Room Supplement Per Request)
** የተጠቀሱት ቀናቶች ሁለት ወደ እስራኤል የመምጫና የመመለሻ ቀናቶችን ይጨምራል (Next Day Arrival)
የጉዞ ቀናቶች*
ዋጋ
ከታህሳስ 27 እስከ ጥር 4, 2017
5 - 12 January, 2025
$ 1,280 per person in Double room
ከታህሳስ 26 እስከ ጥር 6, 2017
5 - 14 January, 2025
$ 1,590 per person in Double room
FAMILY PLAN
Children (0-2) sharing a bed with their parents
Children (2-12) sharing a bed with their parents
Children ( 18 +) sharing a room with their parents
Free
10% Discount
Full Price
See your tour route
Please read the following Important Notes
This website uses cookies to ensure you get the best experience on our website. By using this website, you agree to our use of cookies. We use cookies to provide you with a great experience and to help our website run effectively.